KEMMCOM Media and Communications

በታሸገ ውኃ ላይ ኤክሳይስ ታክስ መጣል የለበትም›› ጌትነት በላይ (ኢንጂነር)፣ የኢትዮጵያ የታሸገ ውኃ፣ የለስላሳ መጠጥ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ አቀነባባሪዎች ኢንዱስትሪ ማኅበር ቦርድ ፕሬዚዳንት

By: ዳዊት ታዬ
Published On: August 29, 2021

የተፈጥሮ ውኃን በአግባቡ መጠቀም አስፈላጊነት ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡ አላቂ ሀብት ነው ተብሎ የሚታመነውን ውኃ በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም ካልተቻለ ወደፊት እጥረት ይፈጠራል የሚል ሥጋትም አለ፡፡ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የውኃ ሀብት አላት ቢባልም፣ በአግባቡ መጠቀም ካልተቻለ የችግሩ ሰላባ ትሆናለች የሚሉ ምልከታዎች እየተንፀባረቁ ነው፡፡ በከፍተኛ ደረጃ ውኃን ዋነኛ ግብዓት አድርገው የሚጠቀሙ ፋብሪካዎች የውኃ እጥረት የሚያጋጥማቸው ወቅት አለ፡፡ ይህ ጉዳይ ዝም ከተባለና ውኃን ቆጥቦ በመጠቀም በጋራም ሆነ በግል መሥራት ካልተቻለ፣ እ.ኤ.አ. በ2030 የውኃ እጥረት ሊያጋጥም ይችላል የሚል በጥናት ላይ የተመሠረተ ትንታኔ ይቀርባል፡፡ ይህ ጉዳይ ኢትዮጵያንም የሚመለከት በመሆኑ ውኃን ዋነኛ ግብዓት አድርገው የሚጠቀሙ እንደ የታሸጉ ውኃ አምራቾች፣ የለስላሳ መጠጥ አምራቾች፣ የአትክልትና ፍራፍሬ አቀነባባሪዎች፣ የቢራ አምራቾች፣ የአልኮልና የወይን አምራቾች ከውኃ እጥረት፣ ብክነትና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በጋራ መሥራት እንዳለባቸው በማመን አንድ ኅብረት እስከ መፍጠር ደርሰዋል፡፡ ይህ ኅብረት ውኃን በአግባቡ ለመጠቀም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሥራት ሥጋቱን ለመቀነስ እንዲቻል ይሠራል ተብሏል፡፡ ባለፈው ሳምንት የተመሠረተውን ኅብረት በመፍጠር ዋነኛ ድርሻ የነበረው ኢትዮጵያ የታሸገ ውኃ፣ የለስላሳ መጠጥ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ አቀነባባሪዎች ኢንዱስትሪ አምራቾች ማኅበር ተጠቃሽ ነው፡፡ ዳዊት ታዬ የታሸገ ውኃ ምርትን ሥጋት እየሆነ ከመጣው ውኃ እጥረት፣ እንዲሁም የማኅበሩን እንቅስቃሴ በተመለከተ የማኅበሩን ቦርድ ፕሬዚዳንት ጌትነት በላይ (ኢንጂነር) አነጋግሯል፡፡